ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የአፍሪካ ቀንድ የአካባቢ ማዕከልና ኔትወርክ – አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ቢሮ ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ግቢ የሚገኙ አገልግሎት የሰጡ የመኪና ጎማዎች፣ መለዋወጫዎችና የቢሮ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ተጫራች ማሟላት ያለበት ዝርዝር መስፈርት እንደሚከተለው ቀርቧል።
- ተጫራቹ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጀውን ያገለገሉ ንብረቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት ጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል ግቢ ውስጥ በሚገኘው የማዕከሉ ዋናው ቢሮ (ማለትም ከሸጎሌ አንበሳ ጋራዥ ፊት ለፊት ከዋናው አስፓልት ተገንጥሎ በሚያስገባው ኮብልስቶን መንገድ ወደ ውስጥ በዋናው በር በመግባት) የጨረታ ሰነድ በመግዛት ሰነድ የገዙበትን ማስረጃ (ደረሰኝ) በማሳየት በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 9፡00ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የንብረት ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሽገ ፖስታ ኦሪጅናል በድርጅቱ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ከመስከረም 20/2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በመጨረሻው ቀን የጨረታ ሳጥኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው ቢሮ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ጥቅል ዋጋ 20 /ሃያ/ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ባስያዘው ሲፒኦ ላይ ቀሪ ክፍያውን በ5 /አምስት/ ቀናት ከፍሎ ንብረቱን በ10 /አስር/ ቀናት ውስጥ ማስነሳት ይኖርበታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን በሲ.ፒ.ኦ. ያስያዘው ገንዘብ ወደ ማዕከሉ ገቢ ይደረጋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው ለእያንዳንዱ የሚወገድ ንብረት ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበና የዋስትና ማስያዣ ካቀረበው ጠቅላላ ዋጋ 20% /ሃያ በመቶ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ያቀረበ ብቻ ነው፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ መሆኑን እየገለፅን ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0911-899779 በስራ ሰዓት ብቻ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡